መጽሐፉ በአሥር ምዕራፎች የተከፋፈለ ሆኖ በክርስትና ሚዛን የዓለምን ቁልፍ የአስተዳደርና ፖለቲካ፥ የማኅበረሰብና የመንፈሳዊ ሕይወት ፈተናዎችንና የኦርቶዶክሳዊነትን እና የኢትዮጵያዊነትን ልዕልና ያመለክታል። የመጽሐፉ አጠቃላይ ጭብጥ የዓለም ማያ ወይም ማኅቀፈ ዕሳቤ (world view) በመቅረጽ ክርስቲያናዊ ማንነትንበሕይወት ለመግለፅ የሚረዱ ጉዳዮችን በማሳየት ክርስቲያኖችን ከዘመኑ ረቂቅ ኑፋቄ ራሱን እንዲጠብቅ ማሳሰብ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሉላዊ የበላይነትን (global superiority) በመያዝ በሰው ልጆች ግላዊ፣ የወልናተቋማዊ ጉዳዮች ውስጥ ክርስቲያናዊም፣ ኢ-ክርስቲያናዊም አስተሳሰቦች ሊንጸባረቁ እንደሚችሉ በማመልከትክርስቲያን ወላጆች ልጆቻቸው፥ የማኅበረሰብ መሪዎች ማኅበረሰባቸውን፥ የአገር መሪዎች የአገራቸውን ዜጎች ከብልሽት የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን በዕውቀት እንዲመሩትና ከጭፍን ገልባጭነት (mindless copying) እና ከጭፍን መንጋነት (groupthink slavery and mob ganging) እንዲጠበቁ ጠንካራ ማሳያዎችን እየጠቀሰና ፍልስፍናዎችን እየሞገተ ይከራከራል። በሌላ በኩል ይህ መጽሐፍ ትውልድን ኢ-ክርስቲያናዊ ለማድረግ የሥዝም ሰብአዊነት ፍልስፍናን በመከተልየበላይነትን የያዙት ኢ-ክርስቲያናዊ አስተምህሮዎች የሚጠቀሙባቸውን ትውልድን ከማንነቱ የማዘናጊያናማንሸራተቻ ስልቶችን በመረዳት ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማንቃትአቅሙ ያላቸው ምሁራንና የተለያዩ ዘርኦች ምሁራንን ምን እየሠራን ነው የሚል ጥያቄ በራሳቸው ላይ እንዲያነሱ ምክረ ሀሳብ ያርባል። በመጨረሻም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፍጹምነትና ይህን ሰማያዊ ገንዘቧን ለማስጣል ዘመኑ የከፈተባትን ጦርነት፥ በተለይ የዘመናችን ፖለቲካና መንግሥት፥ የመንግሥት የውስጥ ተላላኪዎ የሚኣደርሱትን ሁለገብ ጥቃት ለመቋቋም ጸሐፊው መደረግ ይገባዋል ብሎ የሚያምነው አመልከቶ ከረዥም የአገልግሎት ልምድና ከጥናት ተነስቶ አስተያየት ይሰጣል። በአጠቃላይ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የመጣባቸውን ታላቅ ፈተና በመረዳት ወቅቱ የሚጠይቀውን የሰማዕትነት ጉዞ፤ በዚህ በአብዛኛው በሥልጣኔ፣በዘመናዊነት፣ በክርስቲያናዊ መንፈሳዊነት፣ በሳይንሳዊ ግኝት ስም ተሸፍኖ በክህደትና በማኅበራዊ ዳርዊናዊነት የሚመራው ዓለም በኢትዮጵያዊነት ላይ በተለይም በኦርቶዶክሳዊነት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖያብራራል። ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም መዳን የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ፍቱን መድኃኒትነት ምሥጢሩ ለራቃቸውና በቤተክርስቲያን ውስጥ እየኖሩ አጥፊውን ሥዝም ሰብአዊነት የሚናፍቁትን ከስህተታቸው የሚመለሱበትን የንቃ ደወል ድምጽ ያሰማል። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተቋማዊ ኃላፊነትን በተመለከተ አስተያየትና ምክረ አሳብ ያ
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.